የሜዳ አጠቃቀም መመሪያዎች እና የተከራይ ኃላፊነቶች
- አንድ ቡድን በአንድ ሳምንት ውስጥ መከራየት የሚችለው 1 ቀን (ቢበዛ 2 ሰዓት) ብቻ ሲሆን ከዚህ በላይ የሆኑ ፕሮግራሞች ይዞ ቢገኝ ፓርኩ ሙሉ ፕሮግራሙን የሚሰርዝ እና የተከፈለ ክፍያ ተመላሽ አይሆንም።
- ፓርኩ የመጫወቻ ሜዳውን ብቻ የሚያቀርብ ሲሆን፤ ለጨዋታ አስፈላጊ የሆኑ ኳሶችን፣ ኮኖች፣ ትጥቆች እና ሌሎች ጨዋታውን ለማካሄድ አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን የማቅረብ ሃላፊነት የቡድኑ ነው።
- ለመጫወቻው ሜዳ ጥንቃቄ ሲባል ታኬታ ጫማ አድርጎ መጫወት ፈፅሞ የተከለከለ ነው።
- ሜዳውን ከተከራዩ በኋላ ለሌላ ሶስተኛ ወገን ማከራየት ፈፅሞ የተከለከለ ነው፤ ይህ ሆኖ ሲገኝ የፓርኩ አስተዳደር የኪራይ ውሉን የማቋረጥ እርምጃ ይወስዳል።
- የኪራይ ቀን በፓርኩ አስተዳደር የሚወሰን ይሆናል። ፓርኩ ወይም ሜዳው ለመንግስት ዝግጅቶች፣ በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ እና በብልሽት ምክንያት የሚዘጋ ከሆነ ፓርኩ የተያዘ ፕሮግራምን የመሰረዝ እና እንደገና ቀጠሮ የማስያዝ መብት ይኖረዋል። ቡድኖች ፓርኩ በሚሰጣቸው ምትክ ሰዓት (ከምሽቱ 2፡00 - 4፡00 ሰዓት ጨምሮ) የመጫወት ግዴታ አለባቸው።
- ሜዳውን መጠቀም የሚቻለው በስምምነቱ ላይ በተገለፁት ዕለታት እና ሰዓታት ብቻ ነው። ቀደም ብሎ ወደ ሜዳ መግባት ወይም ዘግይቶ ሜዳውን መልቀቅ አይፈቀድም። ፓርኩ ከተስማማው ጊዜ በላይ በሜዳውን ለመጠቀም የሚሞክር ቡድን ወይም ግለሰብ ከሜዳ የማስወጣት እና ስምምነቱን የማቋረጥ እርምጃ ይወስዳል።
- የአልኮል መጠጦች ይዞ መግባት እና አደንዛዥ እፆችን መጠቀም ፈፅሞ የተከለከለ ነው።
- የሜዳው መጠን ቀድሞ የተወሰነ እና ለድርድር የማይቀርብ ነው፤ በምንም መልኩ ሜዳው ላይ መስመሮችን ማስመር፣ ምልክት ማድረግ አይፈቀድም። የግብ ጎሎችን፣ ወንበሮች እና የቆሻሻ ማጠራቀሚያዎች ማንቀስቀስ የተከለከለ ነው።
- ተጠቃሚዎች በሜዳው ላይ ምንም አይነት ጉዳት ከሚያደርሱ ተግባራት መቆጠብ ይኖርባቸዋል። በሜዳው ላይ ጉዳት ደርሶ ሲገኝ ለተበላሹ ቁሶች ጥገና ወጪዎች ተከራይ የሚከፍል ይሆናል።
- የተጫዋቾችን ንብረት ማስጠበቅ የተከራዮች ግዴታ ሲሆን፤ ፓርኩ ለጠፉ ወይም ለተሰረቁ እቃዎች ሃላፊነት የለበትም።
- ተጫዋቾቹ ተገቢውን የስፖርት ትጥቅ ካለበሱ በስተቀር በሜዳው ወስጥ ገብተው መጫወት አይችሉም።
- የፓርኩ የስራ ሃላፊዎች እና ሰራተኞች በማንኛውም ጊዜ እና በማንኛውም አጋጣሚ ያለ ምንም ገደብ ወደ መጫወቻ ሜዳው የመግባት እና የሜዳ አጠቃቀም ሂደቶችን የመከታተል እና የእርምት እርምጃ የመውሰድ መብት አላቸው።
- ወደ ፓርኩ ምንም አይነት ምግብ እና መጠጥ ይዞ መግባት የተከለከለ ሲሆን ቡድኖች ይህንን አገልግሎት ከፈለጉ በፓርኩ ወስጥ ከሚገኙ የአገልግሎት ሰጪዎች መጠቀም ይችላሉ።
- የሜዳ ተከራይ ቡድኖች ከእያንዳንዱ ጨዋታ በኋላ የጣሉትን ቆሻሻ የማጽዳት እና በተገቢው የቆሻሻ መጣያ ቅርጫት ውስጥ የማስቀመጥ ግዴታ ይኖርበታል።
- ያለ ፓርኩ አስተዳደር ፍቃድ የድምጽ ማጉያዎች እና ሌሎች የሙዚቃ መሳሪያዎች ወደ ፓርኩ ይዞ መግባት የተከለከለ ነው።
- በሜዳ ውስጥ መሰዳደብ፣ መደባደብ እና ሌሎችን ወደ ፀብ የሚወስዱ ቃላትን መጠቀም ፈፅሞ የተከለከለ ነው።
- መኪና ይዘው ወደ ፓርኩ የሚገቡ ተጫዋቾች ከኪራይ ክፍያው በተጨማሪ በመኪና 50 ብር የሚከፍሉ ይሆናል።
- ተከራይ ቡድኖች ሙሉ የቡድናቸውን ተጫዋቾች ዝርዝር ለፓርኩ አስተዳደር ኪራዩ በተፈፀመበት ቀን ጀምሮ በሶስት (3) ቀናት ውስጥ የማሳወቅ ግዴታ አለባቸው።
- በአንድ ግዜ ሜዳው ማስተናገድ የሚችለው የተጫዋች ቁጥር 12 ብቻ ሲሆን፤ አንድ ተከራይ ቡድን በአጠቃላይ ሊኖረው የሚችለው የተጫዋች ቁጥር 18 ብቻ መሆኑን አውቄ ተስማምቻለሁ።